Lrc Player

042.Wekidisate Menfes

Unknown artist
[07:57.97]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.

[00:35.99] ወቅድሳተ መንፈስ

[00:46.88] ወሀበነ ማየ መንጽሔ ዚአነ

[01:12.14] ቅድስት ትዕዛዙን አፍርሰን

[01:20.91] ወደ ምድረ ፋይድ ብንወርድ

[01:28.35] በኀጢአት ወጥመድ ተይዘን በሲኦል እሳት ስንነድ

[01:44.81] የምንዱባንን ጩኸት ከሰማይ ሆኖ ሰማና

[01:57.04] በደሙ እንዲቤዥ ዓለሙን አንድያ ልጁን ላከና

[02:18.55] ወቅድሳተ መንፈስ

[02:27.85] ወሀበነ ማየ መንጽሔ ዚአነ

[02:52.56] የሐሰት አባት ሳጥናኤል የፍጥኝ አስሮን በዕዳ

[03:00.27] በዕብነ ሩካብ ጽፎብን የሞት ደብዳቤ የፍዳ

[03:23.38] ነጻ እንዲያወጣን በጥምቀት ከሲኦል ኑሮ ጎዳና

[03:36.40] አበሳችንን ሊያስወግድ ወደ ዮርዳኖስ መጣና

[03:53.67] ወቅድሳተ መንፈስ

[04:04.05] ወሀበነ ማየ መንጽሔ ዚአነ

[04:28.48] ጸጋው ተገፎ የሰው ልጅ ሲኖር በምውት ገዳም

[04:42.81] የጽድቅ ጎዳና ጠፍቶበት ሲናፍቅ ያችን ዓለም

[04:59.81] በአምስተኛው ቀን ከመንፈቅ ብርሃን ከምስራቅ ፈንጥቆ

[05:13.37] አስወገደለት መርገሙን ከዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ

[05:30.63] ወቅድሳተ መንፈስ

[05:39.67] ወሀበነ ማየ መንጽሔ ዚአነ

[06:05.42] አብ ከላይ ሆኖ አሰማ የምስራች ቃል ለሁሉ

[06:18.98] የዕዳ ደብዳቤ ስረዛ ተደርጓልና በሙሉ

[06:34.92] ቀለም አበሳ ተፋቀ ዳግም ተሰጠን ልጅነት

[06:46.88] ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ከላይ ውሃ ደፍቶበት

[07:06.27] ወቅድሳተ መንፈስ

[07:16.36] ወሀበነ ማየ መንጽሔ ዚአነ