Lrc Player

057.Himam Yematawkew

Unknown artist
[05:35.46]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.

[00:08.01] ሕማም የማታውቀው ድካም የሌለብህ

[00:22.01] ስለኛ ተራብህ ደከምህ በእውነት

[00:34.87] የደም ላብ አላበህ ብዙም አስጨነቁህ

[00:48.02] እጅና እግርህን አስረውት አይሁድ አንገላቱህ/፪/

[01:11.46] በቀርክሃ በጅራፍ አምላኬ ገረፉህ

[01:24.33] በፈጠርከው ፍጥረት መወጋት መድማትህ

[01:37.19] ምን ይሆን ምሥጢሩ ያንተ መንገላታት/፪/

[01:59.77] መንፈሳዊ አርበኛ ማርያም መግደላዊት

[02:12.35] ያንተ ሕማም ሞት ያንተ ስቃይ ጨንቋት

[02:24.92] በእኩለ ሌሊት ፅልመቱን ሳትፈራ

[02:37.21] አመጣት ጎትቶ የፍቅርህ አሻራ/፪/

[02:59.22] ያ ሁሉ መከራ እንዴት ይግባ ልቤ

[03:11.81] አልበጠስ አለኝ የኃጢአት መረቤ

[03:24.10] መቼ ይሆን ፍቅርህ ለእኔ የሚገባኝ

[03:36.96] ሕማም ጉስቁልናህ ልቤን የሚነካኝ/፪/

[03:48.39] ቃሉን ተናጋሪ ምግባር የሌለኝ

[04:11.26] ተገርፏል ተሰቅሏል የምል ብቻ ሆንኩኝ/፫/

[04:36.70] ተው ልቤን ስበረው ልመንህ አጥብቄ

[04:47.56] መቼ ሕይወት ሆነኝ ሕግህን ማወቄ

[05:00.71] እባክህ የኔ ጌታ መንፈሴን ስበረው

[05:12.72] የመስቀሉን ፍቅር በልቤ ላይ ሳለው/፪/