184.Amlakehen weded
[00:08.92] በደልህን አምነህ ንስሐ ግባና
[00:16.36] ወደ አምላክህ አልቅስ ተጸጸትና
[00:23.26] አመስግነው ጌታን አፍቅረው ከልብህ
[00:35.64] በጉብዝናህ ወራት በሱ ደስ ይበልህ
[00:40.15] ስትቸገር አይቶ ንቆ የማይተውህ
[00:47.32] አምላክህን ውደድ እሱ ነው አለኝታህ/፪/
[01:01.39] የኀጢአት ኑሮን አቁምና ዛሬ
[01:09.63] ለማፍራት ተነሣ የንስሐ ፍሬ
[01:16.27] የእግዚአብሔርን ድምጽ አትናቅ ጥሪውን
[01:25.31] ተመለስ ይልሃል አስተውል መንገዱን
[01:32.48] ስትቸገር አይቶ ንቆ የማይተውህ
[01:39.65] አምላክህን ውደድ እሱ ነው አለኝታህ/፪/
[01:54.53] የጉብዝናህ ወራት ያበቃል ያከትማል
[02:03.03] ድካም መሸነፍ መውደቅም ይመጣል
[02:10.20] ተስፋህ ይጨልማል ንብረትህም ያልቃል
[02:19.50] ወጣትነትህስ መች ሁሌ ይኖራል
[02:26.94] ስትቸገር አይቶ ንቆ የማይተውህ
[02:34.12] አምላክህን ውደድ እሱ ነው አለኝታህ/፪/
[02:48.20] የወደቅህ ለታ ማንም አያይህም
[02:57.03] ሁሉም ሲኖርህ ነው ከአንተ ጋር አይቆምም
[03:03.93] እስከ መቼ ድረስ እንዲህ ትኖራለህ
[03:12.70] መለከት ሲነፋ ወዴት ትገባለህ
[03:20.14] ስትቸገር አይቶ ንቆ የማይተውህ
[03:27.32] አምላክህን ውደድ እሱ ነው አለኝታህ/፪/
[03:41.93] ለካህኑ ነግረህ የሰራኸውን ኀጢአት
[03:50.42] ቀኖና ተቀበል እንድታገኝ ስርየት
[03:57.33] ቤትህን አዘጋጅ ክርስቶስ ይመጣል
[04:06.90] ማድጋህን ክፈት እሱ ይሞላዋል
[04:14.32] ስትቸገር አይቶ ንቆ የማይተውህ
[04:21.50] አምላክህን ውደድ እሱ ነው አለኝታህ/፪/
[04:35.84] ተመለስ ወደ እርሱ በደሙ ገዝቶሃል
[04:44.34] እርሱም አይቀየር ሊቀበልህ ወጥቷል
[04:50.99] አመስግነው ጌታን አፍቅረው ከልብህ
[05:00.55] በጉብዝናህ ወራት በእርሱ ደስ ይበልህ
[05:07.72] ስትቸገር አይቶ ንቆ የማይተውህ
[05:14.90] አምላክህን ውደድ እሱ ነው አለኝታህ/፪/
