096. Selam lanchi yihun
[02:42.09] ሰላም ለአንቺ ይሁን ቅድስት እናትችን
[02:48.47] የአዳም ልጆች ተስፋ የሰማይ ቤታችን /፪/
[03:15.55] ነቢዩ ሕዝቅኤል የተነበየልሽ
[03:21.14] ከአዳም ዘር መካከል አምላክ የመረጠሽ
[03:26.45] የሥላሴ ዙፋን የተዘረጋብሽ
[03:32.57] ንጽሕት አዳራሽ ተስፋችን አንቺው ነሽ
[03:37.08] ሰላም ለአንቺ ይሁን ቅድስት እናትችን
[03:44.78] የአዳም ልጆች ተስፋ የሰማይ ቤታችን /፪/
[04:11.08] ለሐና ለኢያቄም አንቺን ቢሰጣቸው
[04:17.18] ሁሉን ቻይ የሆነው ቸሩ አምላካቸው
[04:21.97] ወስደው አስረከቡሽ ከቤተ መቅደስ
[04:27.80] ማደሪያ ልትሆኚ ለመንፈስ ቅዱስ
[04:32.87] ሰላም ለአንቺ ይሁን ቅድስት እናትችን
[04:40.02] የአዳም ልጆች ተስፋ የሰማይ ቤታችን /፪/
[05:05.80] የሐና ፍሬዋ የኢያቄም ዘር
[05:11.90] ባንቺ ተከፈተ የተዘጋው በር
[05:17.49] ባንቺ ቅድስና ጸጋን አግኝተናል
[05:23.33] በተሰጠሸ ኪዳን ሕይወትን ወርሰናል
[05:28.38] ሰላም ለአንቺ ይሁን ቅድስት እናትችን
[05:35.01] የአዳም ልጆች ተስፋ የሰማይ ቤታችን /፪/
[06:01.58] በኅሊና አምላክ ቀድሞ የነበርሽ
[06:07.69] ለተከዘው አዳም መፅናኛው የሆንሽ
[06:12.73] ርግማን ደርሶባት ሔዋን ስታነባ
[06:18.84] የብርሃን ጸዳል ሆንሽላት አበባ
[06:23.89] ሰላም ለአንቺ ይሁን ቅድስት እናትችን
[06:32.12] የአዳም ልጆች ተስፋ የሰማይ ቤታችን /፪/
