144 የቅዱሳን በዓት
[00:13.21] ልቦና የሚመስጥ መዓዛ እጣኗ
[00:19.32] ሕሊናን ይገዛል ዝማሬ ድጓዋ
[00:24.90] የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው
[00:31.27] ቤተ ክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያቸው
[00:43.75] የመላእክት ዜማ የአዕዋፍ ዝማሬ
[00:49.34] የሚለቀምባት የትሩፋት ፍሬ
[00:54.65] የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው
[01:00.75] ቤተ ክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያቸው
[01:13.24] ይዘምሩባታል በአንድነት ተባብረው
[01:18.82] የሌዋዊው በትር ፀናፅል ከበሮው
[01:24.66] የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው
[01:30.77] ቤተ ክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያቸው
[01:43.00] ወራዳዋን ዓለም የናቋት በቅድሚያ
[01:48.84] የእምነት አርበኞች ያገኟት በፍልሚያ
[01:53.61] የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው
[02:00.25] ቤተ ክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያቸው
[02:12.74] የገድላቸው ተዓምር መንቦግቦጊያ መቅረዝ
[02:18.32] የሰማዕታት አክሊል የሥራቸው ደሞዝ
[02:23.63] የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው
[02:29.47] ቤተ ክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያቸው
[02:42.22] መውደቂያዬ ይሁን ከመቃብራቸው
[02:47.80] ይፈውሳልና ተረፈ አጽማቸው
[02:53.39] የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው
[02:59.49] ቤተ ክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያቸው
[03:11.70] ከኃጥአን ድንኳን መውጣቴ ነው ዛሬ
[03:17.02] የቅዱሳን በዓት ልትሆነኝ ሀገሬ
[03:22.87] የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው
[03:28.97] ቤተ ክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያቸው
[03:34.82] የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው
[03:40.66] ቤተ ክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያቸው
