Lrc Player

36. እስቲ ላመስግንሽ

Unknown artist
[07:41.24]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.

[00:11.59] እስቲ ላመስግንሽ እንደችሎታዬ/፪/ /፪/

[00:40.06] አንቺ ነሽ እመ አምላክ ዋሴ ጠበቃዬ/፪/

[01:07.76] ሰማይና ምድርን በቃሉ ያጸና /፪/

[01:22.92] ከሥጋሽ ከነፍስሽ ተዋሕዷልና /፪/

[01:35.40] ድንግል ይገባሻል ውዳሴ ምስጋና/፪/

[02:02.76] ምሕረት እንድናገኝ በነፍስም በሥጋ/፪/

[02:29.89] ወደ ጌታዬ እናት እጆቼን ልዘርጋ/፪/

[02:48.40] ዕፀ ሕይወት ዛፍ ነሽ ፍሬሽ መድኃኒት /፪/

[03:14.32] በአንቺ ያመነ ሰው የለበትም ሞት/፪/

[03:41.97] ድንግል በረድኤትሽ የባረክሽው ሁሉ /፪/

[04:08.00] ያድርበታልና የመለኮት ኃይሉ/፪/

[04:26.33] እንድታሻግሪን ከጥፋት ባሕር/፪/

[04:52.36] አደራሽን ቅድስት የአምላክ ማኅደር/፪/

[05:19.71] ድክመቴን እያየ ሰይጣን ሲደነፋ /፪/

[05:47.06] እመቤቴ አያለች እኔ አልቆርጥም ተስፋ/፪/

[06:04.05] ስምሽም ያነፃል ከኃጢአት እድፍ /፪/

[06:29.28] የጌታዬ እናት በአንቺ ልደገፍ /፪/