Lrc Player

38. የሕይወት መሰላል

Unknown artist
[05:35.69]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.

[00:01.22] ድንግል ሆይ /፪/ የአምላክ ማህደር

[00:25.39] ተተክላ የቆመች ከምድር እስከ ሰማይ

[00:36.28] የሕይወት መሰላል በጽድቅ የምትታይ

[00:47.16] የወጡባት የወረዱባት መላእክተ/፪/ ሰማይ

[01:00.98] ድንግል ሆይ /፪/ ምሳሌዋ አንቺ ነሽ /፪/

[01:40.05] በቅድስና ያጌጠች የንፁህ ዕጣን ሙዳይ

[01:50.93] ጸሎት ማሳረጊያ ወደ አምላክ አዶናይ

[02:01.82] ንፁህ መዓዛቸው ለመላእክተ ሰማይ

[02:14.84] ድንግል ሆይ /፪/ የወርቅ ማዕጠንት /፪/

[02:53.88] ለምልማ የተገኘች የአሮን በትር

[03:04.51] ውኃ ሳያጠጧት ሳይተክሏት በምድር

[03:16.72] አብባ ያፈራች ያለወንድ/፪/ ዘር

[03:28.41] ድንግል ሆይ /፪/ የአምላክ ማኅደር /፪/

[04:07.67] በዚያች ቤተልሔም በግርግሙ ስፍራ

[04:18.55] ሰብአ ሰገል ሰግደዋል ገብተው በየተራ

[04:29.43] በእቅፍሽ ስላዩ የሕይወትን/፪/ እንጀራ

[04:42.45] ድንግል ሆይ /፪/ የተስፋ አዝመራ /፪/