Lrc Player

39. ማርያም ድንግል

Unknown artist
[04:57.98]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.

[00:01.19] ማርያም ድንግል ጸልዪ /፫/ ድንግል ለመላው ዓለም /፪/

[00:37.07] እንዲያገኝ ሰላም /፬/ ጸልዪ ድንግል ማርያም ለመላው ዓለም

[01:02.91] የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶልሻልና ከአንቺ የተወለደው መድኃኔዓለም/፪/

[01:35.52] ቃል እንደ ገባለት ቀድሞ ለአዳም /፪/

[01:51.04] ተሰቅሎ ያድነው ዘንድ በፍቅሩ ፍጹም

[01:59.26] የሕይወት መሰላል ነሽ የዳዊት መሰንቆ የሰሎሞን አክሊል የሴም ቡራኬው /፪/

[02:32.51] የሙሴ ጽላት ነሽ የአዳም ተስፋው /፪/

[02:48.35] ከገነት በወጣ ጊዜ ዞሮ መግቢያው

[02:55.77] በስድስተኛው ወር ወደ አንቺ ተልኮ እንዳመሰገነሽ ገብርኤል በቃሉ /፪/

[03:27.01] ያመሰግኑሻል ትውልድም በሙሉ /፪/

[03:42.73] እንደተጻፈ በወንጌሉ ብጽዕት እያሉ

[03:51.23] የነቢያት ትንቢት የቅዱሳን ተስፋ ያቺ የጽድቅ በር ሕዝቅኤል ያያት /፪/

[04:21.62] የአሮን በትር ነሽ ዕፀ መድኃኒት /፪/

[04:37.31] አማልጅን ኪዳነ ምሕረት ዳግመኛ እንዳንሞት /፪/