45. ኆኅት አንቲ
[00:22.96] ኆኅት አንቲ ለፀሐየ ጽድቅ /፪/ ምሥራቁ
[00:37.37] እንተ ባቲ ሠረቀ ለብርሃነ ዓለም ጽድቁ /፪/
[01:04.24] የተዘጋችው በር የምሥራቋ ደጃፍ
[01:11.68] የታተመች ገነት የሐዲስ ዘመን ምዕራፍ
[01:19.79] ሌቱ ያለፈብሽ የተስፋ ማለዳ
[01:27.49] በልጅሽ ተፋቀ መርገምና ፍዳ/፪/
[01:45.53] ኆኅት አንቲ ለፀሐየ ጽድቅ /፪/ ምሥራቁ
[01:57.01] እንተ ባቲ ሠረቀ ለብርሃነ ዓለም ጽድቁ /፪/
[02:22.39] ጨለማን የሻረ የጽድቅ ጎሕ ፋና
[02:31.02] የሐዲስ ታሪክ ቀለም የእረፍታችን ዜና
[02:37.79] ሥጋሽ ሰውነቱ ነፍስሽ ነፍሱ ሆነ
[02:45.16] ድል አድራጊው ልጅሽ ጠላትን በተነ /፪/
[03:09.31] የእውነት ምንጭ ነሽ የደስታ መፍሰሻ
[03:16.75] የኃያሉ ንጉሥ መንበር መናገሻ
[03:23.92] ንጽሕና ተውበሽ በቀኙ ስትቆሚ
[03:31.62] ባዶ የሚሞላ ድምፅሽን አሰሚ /፪/
[03:55.77] ኃዘን መጨነቁ በምድር ሲበዛ
[04:03.20] ከልጅሽ አሳስበሽ አድርጊልን ጤዛ
[04:10.38] የተስፋ ወጋገን ምሕረትን አሳይን
[04:17.55] እመብርሃን ጸዳል ለምስጋና አብቂን/፪/
[04:33.56] ኆኅት አንቲ ለፀሐየ ጽድቅ /፪/ ምሥራቁ
[04:46.16] እንተ ባቲ ሠረቀ ለብርሃነ ዓለም ጽድቁ /፪/
