20. እሳት ጽርሑ
[00:10.52] እሳት ጽርሑ ማይ ጠፈሩ/፪/
[00:24.06] ደመና መንኮራኩሩ ለመድኃኔዓለም/፪/
[01:00.50] ነፋስን ሰውረህ ድምፅን የምትሰጠው
[01:07.95] ጉምን ያለ ጩኸት የምታስሔደው
[01:16.17] ዙፋኑን ያጠረ በእሳት የጋረደ
[01:23.61] እንዳንተ ማን አለ በጥበብ የሔደ
[01:31.58] ደመና መንኮራኩሩ ለመድኃኔዓለም/፪/
[01:49.67] ምድርን ያለካስማ መዘርጋት የምትችል
[01:57.40] ያለመወጠሪያ ሰማይን የምትሰቅል
[02:05.65] አእላፋት መላእክት ፊትህ የሚቆሙ
[02:13.09] አንተን ለማመስገን ሁሉም የሚደክሙ
[02:21.07] ደመና መንኮራኩሩ ለመድኃኔዓለም/፪/
[02:38.87] ቀኝ እጅህ እሳት ነው ቃልህ የማይፈርስ
[02:47.38] ለግዛትህ ስፋት የማይደረስ
[02:55.34] አድሎ የሌለብህ ለሀብታም ለድሃ
[03:02.53] ቃልህ አይለወጥ የምትሰጥ ፍስሓ
[03:10.76] ደመና መንኮራኩሩ ለመድኃኔዓለም/፪/
[03:28.55] የተሰወረውን ገልጠህ የምታይ
[03:36.54] በቃልህ የጸኑ ምድርና ሰማይ
[03:44.26] ውኃን በደመና መቋጠር የምትችል
[03:54.09] እንዳንተ ማን አለ የኃያላን ኃያል
[04:00.45] እሳት ጽርሑ ማይ ጠፈሩ/፪/
[04:13.21] ደመና መንኮራኩሩ ለመድኃኔዓለም/፪/
