Lrc Player

30.ተፈጸመ አለ

Unknown artist
[07:13.96]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.

[00:02.30] ተፈጸመ አለ ጌታ ነፍሱን ሰጠ

[00:10.27] ስለ እኔ ኃጢያት በመከራ አለፈ

[00:18.50] በግፍ ተሰቃየ ፍዳን ተቀበለ

[00:27.52] ተሰድቦ ተገርፎ በእንጨት ተሰቀለ

[00:36.56] ደፋ ቀና እያለ ሲወድቅ ሲንገላታ

[00:45.31] የብርሃን ፊቱን በጥፊ ተመታ

[00:54.09] ተፈጸመ አለ ጌታ ነፍሱን ሰጠ

[01:02.85] ስለ እኔ ኃጢያት በመከራ አለፈ

[01:11.36] በሐሰት ተከሶ በሐሰት ተገደለ

[01:20.40] በፍርድ ሸንጎ ፊት በአደባባይ ዋለ

[01:28.90] በውሃ ጥም ዛለ በርሃብ ተቀጣ

[01:37.67] ስለ ሰው ልጆች ሲል የሞት ፅዋ ጠጣ

[01:46.44] ተፈጸመ አለ ጌታ ነፍሱን ሰጠ

[01:55.19] ስለ እኔ ኃጢያት በመከራ አለፈ

[02:04.22] አንቺ ዕለተ አርብ እንዴት ያለሽው ነሽ

[02:13.00] ሰማያዊው አባት የተሰቀለብሽ

[02:21.76] ከኋላው ከፊቱ በጠላት ተከቦ

[02:30.79] ማንም አልነበረም የሚያፅናናው ከቶ

[02:39.29] ተፈጸመ አለ ጌታ ነፍሱን ሰጠ

[02:48.05] ስለ እኔ ኃጢያት በመከራ አለፈ

[02:56.82] ርኅሩኅ ጌታዬ ስለኔ ብለህ ነው

[03:05.06] ያን ሁሉ መከራ በትዕግስት ያለፍኽው

[03:13.84] ኅሩኅ ጌታዬ ስለኔ ብለህ ነው

[03:22.34] ያን ሁሉ መከራ በትዕግስት ያለፍኽው

[03:30.84] ተፈጸመ አለ ጌታ ነፍሱን ሰጠ

[03:39.61] ስለ እኔ ኃጢያት በመከራ አለፈ