15. በሰማይ ለሚኖር
[00:02.47] በሰማይ ለሚኖር ለአምላካችን
[00:11.53] ምስጋና ይድረሰው ከሁላችን /፪/
[00:35.97] እናስታውሰው በጠዋት በማታ
[00:43.14] ብዙ ነውና የእርሱ ውለታ
[00:50.57] መሐሪ ይቅር ባይ ከጥንቱ
[00:57.78] እጅግ ብዙ ነው ምሕረቱ
[01:04.15] በሰማይ ለሚኖር ለአምላካችን
[01:13.44] ምስጋና ይድረሰው ከሁላችን /፪/
[01:21.96] ላበላን ህብስቱን ሥጋውን
[01:28.86] ላጠጣን ጽዋዐ ደሙን
[01:35.25] ለታረዝነው ለኛ ልብሳችን
[01:42.68] ለሰጠን የዕለት ምግባችን
[01:49.06] በሰማይ ለሚኖር ለአምላካችን
[01:58.89] ምስጋና ይድረሰው ከሁላችን /፪/
[02:07.38] በደላችን ሁሉ ለታገሰን
[02:14.61] እስካሁንዋ ሰዓት ላደረሰን
[02:21.27] እናቅርብ ምስጋና ለጌታ
[02:28.75] እንዘምርለት በእልልታ
[02:35.16] በሰማይ ለሚኖር ለአምላካችን
[02:44.75] ምስጋና ይድረሰው ከሁላችን /፪/
[02:52.48] ወድቀን የነበርነው በኃጢአት
[03:00.19] መልሶ አስገባን ከገነት
[03:06.60] ሁሉን ቻይ ነውና ገናና
[03:13.78] ለስሙ ይሁን ምስጋና
[03:20.14] በሰማይ ለሚኖር ለአምላካችን
[03:29.99] ምስጋና ይድረሰው ከሁላችን /፪/
