60. የስደት ዘመንሽ
[00:19.76] መከራን ታግሰሽ ገሊላ የገባሽ ፣
[00:34.63] ለዓለም መፅናኛ ነው የስደት ዘመንሽ ፡፡
[00:56.44] በጠላት ፈተና ከሀገር ተሰደሽ ፣
[01:10.80] ስትንከራተቺ አምላክን ታቅፈሽ ፣
[01:21.96] ከገሊላ አንስቶ እስከ ግብፅ በረሃ ፣
[01:34.72] የሚያዝንልሽ አጣሽ የሚሰጥሽ ዉኃ ፡፡
[01:42.42] መከራን ታግሰሽ ገሊላ የገባሽ ፣
[01:58.10] ለዓለም መፅናኛ ነው የስደት ዘመንሽ ፡፡
[02:18.90] ሰሎሜ ትመስክር ያየሽውን ጭንቀት ፣
[02:32.44] ዮሴፍም ይናገር የሀዘንሽን ብዛት ፣
[02:43.33] እመቤቴ ማርያም ከአንድ ልጅሽ ጋራ ፣
[02:55.55] በግብፅ በረሃ ያየሽዉ መከራ ፡፡
[03:06.97] መከራን ታግሰሽ ገሊላ የገባሽ ፣
[03:19.45] ለዓለም መፅናኛ ነው የስደት ዘመንሽ ፡፡
[03:39.91] ውርጭና ፀሐዩ ሲፈራረቅብሽ ፣
[03:53.19] ረሀብና ጥሙ እንዲያ ሲያንገላታሽ
[04:04.35] በለጋነት ዕድሜ በሄሮድስ ቅናት ፣
[04:16.83] ከልጅሽ ጋር አየሽ መከራ ስደት ፡፡
[04:27.99] መከራን ታግሰሽ ገሊላ የገባሽ ፣
[04:39.94] ለዓለም መፅናኛ ነው የስደት ዘመንሽ ፡፡
[05:01.19] ልጅሽ አንዲምረን ስለእኛ እንዲራራ ፣
[05:14.21] ለበረከት ሆነ ያየሽው መከራ
[05:24.84] መልካም ፍሬ አፈራ ያነባሽው ዕንባ ፣
[05:37.05] ምክንያት ለኛ ሆነ ገነት እንድንገባ ፡፡
[05:47.94] መከራን ታግሰሽ ገሊላ የገባሽ ፣
[06:00.69] ለዓለም መፅናኛ ነው የስደት ዘመንሽ ፡፡
