Lrc Player
72. ዐይኑ ዘርግብ
Unknown artist
[04:53.81]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.
[00:00.92] ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሊቀ መላእክት ሚካኤል
[00:27.24] ልዑለ መንበር ሐመልማለ ወርቅ ሰአሌ ምሕረት ወመተንብል
[00:51.15] ረዳኤ ምንዱባን ዘአስተዓፀቡ ያቀልል
[01:11.89] በእነ ሰናክሬም ላይ ሰይፍን የመዘዘ
[01:24.37] የሕዝቅያስ ምሕረት በእጁ የተያዘ
[01:37.39] መዓቱን ለአሕዛብ በሞት የገለጠ
[01:49.08] የሕዝቅያስን ሞት በሕይወት የለወጠ
[02:09.79] የእስራኤል ድንኳኖች በደስታ ተሞሉ
[02:20.70] ክብር ለአምላካችን ይገባል እያሉ
[02:33.45] መልአኩን የላከ ሕዝቡንም የረዳ
[02:44.35] ግሩም ነው እግዚአብሔር ያወጣን ከዕዳ
[03:05.33] የሰናክሬም ቁጥሩ እጅጉን ብዙ ነው
[03:15.96] የእኛ ረዳት ግን ቅዱስ ሚካኤል ነው
[03:28.44] ከፈረሰኞቹ በላይ ነው ፍጥነቱ
[03:39.06] ከተዋጊዎችም ይበልጣል ብርታቱ
[04:00.05] እስራኤልን መና እንደ መገባቸው
[04:10.41] ባሕታውያንን በዱር የረዳቸው
[04:22.37] ተክለሃይማኖትን ከጉድጓድ ያወጣ
[04:32.98] እኛንም ሳይንቀን ሊያድነን መጣ
