Lrc Player

73. ይኽ ነው ሚካኤል

Unknown artist
[06:20.62]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.

[00:03.02] ይህ ነው ሚካኤል ከመላእክት አንዱ

[00:08.32] መጣልን ሊረዳን ሊያጸናን በክንዱ

[00:15.28] ይህ ነው ሚካኤል ከመላእክት አንዱ

[00:21.93] መጣልን ሊረዳን ሊያጸናን በክንዱ

[00:29.12] የእስራኤል የጉዞአቸው መሪ የማይታክት

[00:37.34] የሚመግብ መና እያወረደ ከሰማያት

[00:45.66] ለኃጥአን ሥርየት እስከሚላክ ከአምላኩ

[00:53.90] ተንበርክኮ ምሕረት ይለምናል መልአኩ

[01:01.60] ይህ ነው ገብርኤል ከመላእክት አንዱ

[01:08.26] መጣልን ሊረዳን ሊያጸናን በክንዱ /፪/

[01:15.17] መላእክትን በጽርሐ አርያም ያረጋጋ

[01:23.40] ለአዳም ልጆች ደስታን ለማብሠር የሚተጋ

[01:31.62] ፈጥኖ መጣ ተልኮ ከሰማይ ከፈጣሪ

[01:39.07] ሊታደገን የሐዲሱ ዜና አብሳሪ

[01:51.83] ይህ ነው ሩፋኤል ከመላእክት አንዱ

[01:57.76] መጣልን ሊረዳን ሊያጸናን በክንዱ /፪/

[02:01.48] ይሰጠናል ለኛ ለሰው ልጆች ሰላምና ጤና

[02:09.97] የተሾመ መንፈሳዊ ሐኪም ነውና

[02:17.41] ሴቶች ሁሉ በፀነሱ ጊዜ ቢማጸኑት

[02:25.66] አይዘገይም ፈታሔ ማኅጸን በዚያች ዕለት

[02:33.90] ይህ ነው ዑራኤል ከመላእክት አንዱ

[02:40.81] መጣልን ሊረዳን ሊያጸናን በክንዱ /፪/

[02:47.45] ግሩም መልአክ በመብረቅ ነጎድጓድ ሥልጣን ያለው

[02:56.48] የሚመጥን የፀሐይን ብርሃን እርሱ እኮ ነው

[03:04.45] በብርሃን ጽዋ ከአምስቱ ችንካሮች እየቀዳ

[03:12.68] አድኖናል ከኃጢአት ከመርገም ከፍዳ

[03:20.39] ይህ ነው ራጉኤል ከመላእክት አንዱ

[03:27.03] መጣልን ሊረዳን ሊያጸናን በክንዱ /፪/

[03:33.95] አጋንንትን በረቂቅ ሥልጣኑ የሚበቀል

[03:42.45] ከከበሩት መላእክት አንዱ ነው ራጉኤል

[03:49.62] የሰው ልጆች በጥልቁ ጨለማ እንዳይኖሩ

[03:58.11] የሚማፀን ከአምላኩ ፊት ቆሞ ከመንበሩ

[04:06.53] ይህ ነው ፋኑኤል ከመላእክት አንዱ

[04:13.18] መጣልን ሊረዳን ሊያጸናን በክንዱ /፪/

[04:20.36] ኤልያስን የረዳው መልአክ ነው ፋኑኤል

[04:28.59] በስደት ላይ ከክፉ በቀሏ ከኤልዛቤል

[04:36.83] ጽዋ ሕይወት ኅብስተ በረከት አምላክ ፈቅዶ

[04:45.06] ፈጥኖ መጥቶ ክንፎቹን አንጥፎና ጋርዶ

[04:52.82] ለአምላክ እናት አብልቶ ያጠጣት ከላይ ወርዶ

[05:01.04] ይህ ነው ሳቁኤል ከመላእክት አንዱ

[05:08.12] መጣልን ሊረዳን ሊያጸናን በክንዱ /፪/

[05:14.22] ቅዱስ መልአክ ቅሩበ እግዚአብሔር ባለሟል

[05:22.55] ወዳጆቹን ወደ ሕይወት መንገድ ይመራል

[05:30.26] ደመናትን የሚያመላልሰው ለዓለማት

[05:37.96] የሚያወጣ ከመዛግብታቸው በነፋሳት

[05:46.47] ሳቁኤል ነው ተወካፌ መሥዋዕት ወጸሎት

[05:54.70] ይህ ነው ሳቁኤል ከመላእክት አንዱ

[06:01.07] መጣልን ሊረዳን ሊያጸናን በክንዱ /፪/