Lrc Player

76. አባ ጊዮርጊስ

Unknown artist
[07:07.13]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.

[00:18.19] የጋስጫው ጻድቅ አባ ጊዮርጊስ

[00:37.58] የሐይቁ መናኒ ምሉዓ ሞገስ

[00:54.07] የድንግል ምስጋና ሰዓታትን ሲያደርስ

[01:10.28] ረቦበት ነበር ቅዱሱ መንፈስ

[01:23.02] ሰአል ለነ አባ ጊዮርጊስ

[01:43.76] የድንግል ማርያም አማላጅነቷ

[02:01.81] ለጋስጫው ጻድቅ ደርሶት በረከቷ

[02:17.75] ጸጋን የተመላሽ ብሎ አመሰገናት

[02:33.18] እንደ ቅዱስ ያሬድ ዜማ ተገልጦለት

[02:48.05] ለምንልን አባ ጊዮርጊስ

[03:07.71] በሱራፌል ቋንቋ በኪሩቤል ልሳን

[03:26.03] ንዒ ንዒ እያለ እየጠራ ስሟን

[03:42.78] በጾም በጸሎቱ ድንግልን ሲማጸን

[03:57.92] ባርካ አጠጣችው ሰማያዊ ጽዋን

[04:11.75] ሰአል ለነ አባ ጊዮርጊስ

[04:34.60] በመላእክት ዜማ በረቂቅ ምሥጢር

[04:52.94] በአስተዋይ ልቦና ተመልቶ በፍቅር

[05:07.28] ማን አመሰገነ እንደ አባ ጊዮርጊስ

[05:21.36] ድንግል ማርያምን በሥጋና በነፍስ

[05:34.11] ለምንልን አባ ጊዮርጊስ

[05:53.77] በድንግል ቃል ኪዳን በአምላክ በረከት

[06:07.86] ተመልተሃልና ጥበብና እምነት

[06:23.55] ለቤተ ክርስቲያን ሆንክላት ማኅቶት

[06:38.70] በውስጧ እንድንኖር ጸንተን በትምህርት

[06:51.19] ሰአል ለነ አባ ጊዮርጊስ