Lrc Player
78. ያሬድ
Unknown artist
[03:51.87]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.
[00:01.20] ምሥጢር ሰማያዊ ከአርያም ከራማ
[00:07.84] ምሥጢር ሰማያዊ ከአርያም ተሰማ
[00:15.82] ያሬድ ማኅሌታይ መሠረተ ዜማ
[00:33.36] ቀድሞ ያልተሰማ ለአንተ የተቸረ
[00:41.32] መንፈሳዊ ጥበብ ከአንተ ተነገረ
[00:50.09] የነፍስ ምግብ ነው የአጥንት ልምላሜ
[01:00.73] ክብረ ሱራፌልን በአንተ አየሁ ደግሜ
[01:18.54] ብሉይና ሐዲስ አስተሳስሮ ነግሮ
[01:26.78] መውረድ መወለድን በቅኔ አመሥጥሮ
[01:35.01] ዘመደ መላእክት የኢትዮጵያ ግርማ
[01:45.37] ያሬድ ጥዑመ ቃል ዘሱራፌል ዜማ
[02:02.91] ምድርና ሰማይን እንዳቆመ ካስማ
[02:10.87] ቤተ ክርስቲያን በሰማይ በራማ
[02:19.37] የሚለውጥ ምሥጢር የሚያራራ ዜማ
[02:29.21] መሠረትህ ፀንቶ ለዓለም ተሰማ
[02:46.48] ተነጥቆ ከምድር አርያም ደረሰ
[02:54.71] ዔረር የሰማውን በምድር አፈሰሰ
[03:02.68] የዓምደ ወርቁ ግርማ የማኅሌቱ ውበት
[03:12.51] ክብርህ የበዛ ነው ያሬድ የዜማ አባት
[03:23.94] ምሥጢር ሰማያዊ ከአርያም ከራማ
[03:31.90] ምሥጢር ሰማያዊ ከአርያም ተሰማ
[03:39.87] ያሬድ ማኅሌታይ መሠረተ ዜማ
