52. ኑ እናድንቅ
[00:17.69] በሁሉም ፍጥረታት በምንም አምሳያ
[00:27.25] ማግኘት አይቻልም የእርሷን አርአያ
[00:39.99] ኑ እናድንቅ ድንግልን የሁላችን መመክያ
[00:49.29] እንደ አባ ሕርያቆስ እንደ ኤጲስ ቆጶሱ
[01:00.45] እንደ ቅዱስ ኤፍሬም ፍሉሕ በመንፈሱ
[01:14.29] እናድንቅ ድንግልን እንዘምርላት
[01:25.97] ሕፀፅ የሌለባት ምልዕተ ጸጋ ናት።
[01:49.61] በሰማይ እንዳንል ሰማይ ነው ዙፋኔ
[01:59.45] የእግሬ መረገጫ ምድሪቱም ናት ለኔ
[02:12.99] ምን አይነት ነው ለኔ የምትሰሩልኝ ቤት
[02:23.61] ብሎ ላለዉ አምላክ ሆናዋለች እናት
[02:35.30] የድንግል መዓዛ የልቧ ንፅሕና
[02:53.09] እመ አምላክ ለመሆን አብቅቷታልና
[03:06.11] እንደ ቅዱስ ያሬድ እንደ አባ ጊዮርጊስ
[03:16.46] እንዘምር በደስታ ክብሯን እናወድስ
[03:39.05] በአርባዕቱ እንስሳ የተያዘ መንበር
[03:49.93] የእሳት መጋረጃ የመለኮት ክብር
[04:03.21] ወዴት ተዘረጋ ወዴት ተጋረደ
[04:13.85] መለኮት ድንግልን ምንኛ ወደደ
[04:31.90] ዳግሚት አርያም የዓለም መዳኛ
[04:43.07] የመላእክት እኅት የሔዋን መጸናኛ
[04:56.88] ታናሽ ብላቴና የንጉሥ ሀገሩ
[05:08.83] ድንግል ማርያም ናት የአምላክ ማኅደሩ
[05:25.83] በሁሉም ፍጥረታት
