Lrc Player
53. ትምክህተ ዘመድነ
Unknown artist
[05:19.09]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.
[00:26.47] ትምክህተ ዘመድነ /፬/ ማርያም እምነ/፪/
[00:37.90] ማርያም ትምክህተ ዘመድነ
[01:04.40] የድኅነታችን አርማ የነፃነታችን
[01:11.04] የሕይወት መሠረት ነሽ ድንግል እናታችን
[01:18.74] አንቺን ለኛ ዘርን ባያስቀር
[01:24.85] እንደ ጥንቱ እንደ ሰዶም ምድር
[01:30.69] ሁላችን በጠፋን ነበር፡፡
[01:59.64] የአብርሐም ድንኳን ነሽ አምላክ ያደረብሽ
[02:04.95] የጌዴዎንም ፀምር ለይቶ ያከበረሽ
[02:12.15] የእኛ ቤዛ በጉ የተያዘብሽ
[02:17.45] የዋህ ርግብ ከአበው ስር የተገኘሽ
[02:23.60] ዕፀ ሳቤቅ የሕይወት ሐረግ ነሽ
[02:50.98] አምላክ ከሰማይ ሆኖ ይህችን ዓለም ሲቃኝ
[02:58.15] ንጽህት ቅድስት ሆነሽ ማርያም አንችን ቢያገኝ
[03:05.59] ትህትናሽን ሕይወትሽንም ወዶ
[03:11.71] ቃል ሰው ሆነ ከሰማያት ወርዶ
[03:17.28] አከበረሽ በፍጹም ተዋሕዶ
[03:45.44] የመዳናችን ምክንያት የሰው ልጆች ሰላም
[03:52.88] ከኃጢአት ከመርገም የዳነብሽ ዓለም
[04:00.58] አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን
[04:06.17] በሲኦል ውስጥ ተግዘን የኖርን
[04:12.01] ድንግል በአንቺ ነጻነት አገኘን
