Lrc Player

58. የለመለመች ዕፅ

Unknown artist
[04:35.51]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.

[00:00.39] የለመለመች ዕፅ የምትጥም ፍሬ

[00:07.31] ከሐና ከኢያቄም ተወለደች (፪) ዛሬ(፪)

[00:34.13] የወርቅ ቀለም ነሽ ያስገኘሽ ወንጌልን

[00:44.75] ተሸክመሽ የዞርሽ መከራ መስቀሉን

[00:53.52] ፀሐይን አወጣሽ ሰማይን መሰልሽው

[01:04.14] ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ጌታን ተሸከምሽው

[01:12.91] የለመለመች ዕፅ የምትጥም ፍሬ

[01:24.07] ከሐና ከኢያቄም ተወለደች (፪) ዛሬ(፪)

[01:30.73] የእንጀራ መገኛ ኮከብን የወለድሽ

[01:40.56] ርኁባነ ሥጋን አብልተሽ ያጠገብሽ

[01:49.58] ባንቺ ላይ አደረ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ

[01:59.96] በማኅጸንሽ ሲያድር ሰማያዊ ንጉሥ

[02:08.98] የለመለመች ዕፅ የምትጥም ፍሬ

[02:16.18] ከሐና ከኢያቄም ተወለደች (፪) ዛሬ(፪)

[02:26.01] የሙሴ ጽላት ነሽ የማደሪያው ታቦት

[02:36.64] ንጽሕተ ንጹሓን ማኅደረ መለኮት

[02:45.42] ገራህተ አብርሃም ጥዑም የወይን እሸት

[02:56.04] የልዩ ኅብር ጌጥ የዓለም መድኃኒት

[03:04.81] የለመለመች ዕፅ የምትጥም ፍሬ

[03:12.24] ከሐና ከኢያቄም ተወለደች (፪) ዛሬ(፪)

[03:22.07] የአዳም የክብሩ ልብስ የከደንሽ እርቃኑን

[03:32.42] ማርኮ ወጣ ልጅሽ ከሲኦል ነፍሳትን

[03:41.46] በልጅሽ ደም ደርቋል የኃጢአት ቁስላችን

[03:51.84] በለምፅ የነደደው ያ ከንቱ ሥጋችን

[04:00.87] የለመለመች ዕፅ የምትጥም ፍሬ

[04:08.04] ከሐና ከኢያቄም ተወለደች (፪) ዛሬ(፪)