Lrc Player

53. ትምክህተ ዘመድነ

Unknown artist
[05:19.09]·Synced by Guest·
This lyric sheet isn't paired with a song yet, so lines are shown but won't sync or seek.

[00:25.96] ትምክህተ ዘመድነ /፬/ ማርያም እምነ/፪/

[00:36.58] ማርያም ትምክህተ ዘመድነ

[01:03.93] የድኅነታችን አርማ የነፃነታችን

[01:11.37] የሕይወት መሠረት ነሽ ድንግል እናታችን

[01:18.81] አንቺን ለኛ ዘርን ባያስቀር

[01:24.65] እንደ ጥንቱ እንደ ሰዶም ምድር

[01:30.78] ሁላችን በጠፋን ነበር፡፡

[01:57.86] የአብርሐም ድንኳን ነሽ አምላክ ያደረብሽ

[02:01.05] የጌዴዎንም ፀምር ለይቶ ያከበረሽ

[02:12.39] የእኛ ቤዛ በጉ የተያዘብሽ

[02:17.96] የዋህ ርግብ ከአበው ስር የተገኘሽ

[02:24.08] ዕፀ ሳቤቅ የሕይወት ሐረግ ነሽ

[02:51.18] አምላክ ከሰማይ ሆኖ ይህችን ዓለም ሲቃኝ

[02:58.08] ንጽህት ቅድስት ሆነሽ ማርያም አንችን ቢያገኝ

[03:05.52] ትህትናሽን ሕይወትሽንም ወዶ

[03:11.36] ቃል ሰው ሆነ ከሰማያት ወርዶ

[03:17.74] አከበረሽ በፍጹም ተዋሕዶ

[03:45.09] የመዳናችን ምክንያት የሰው ልጆች ሰላም

[03:53.07] ከኃጢአት ከመርገም የዳነብሽ ዓለም

[04:00.51] አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን

[04:06.35] በሲኦል ውስጥ ተግዘን የኖርን

[04:12.45] ድንግል በአንቺ ነጻነት አገኘን